[...]"ፕሮፖዛል ኣለኝ።" ምንም እንኳን የትኛውም ምስጢሮችዋ ጥሩ ባይሆኑም ወይንም ደሞ የእውነት ምስጢር ባይሆኑም፣ ልክ ጓደኛዬ ኤፕሪል ምስጢር ለመንገር ስትፈልግ እንደምትሆኖው ወደፊት ዘምበል ኣለች። "እኔ እዚ እንዳሎህ ለማንም ካልተናገርክ፣ ዓይንኖችህን ማስተካከል እችላሎህ።"
"ህጂ ወደዛ!"
ለተወሰነ ግዜ ብልጭ ብልጭ ኣለች! "ኣዎ፣ ለማድረግ እየሞከርኩ ያለሁኝ እሄንን ነው።"
"እኔ'ኮ እሄንን ማድረግ ኣትችይም ማለቴ ነው!"
"ለምንድ ነው እሄንን ማድረግ ማልችለው?"
"ጥሩ፣ በመነጸር ካልሆነ በስተቀር ማንም ሰው ዓይኖቼን ልያስተካክልልኝ የሚችል ሰው ስለሌለ ነው።"
"ደህና፣ እኔ ልዩ ችሎታውች ኣሉኝ። ታያለህ፣ ግን. . ."
"ስላንቺ ለማንም ሰው ካልተናገርኩ ነው?"
"ዋናው ነገር እሱ ነው፣ ፍሬ ነገሩም እሱ ነው።"
"ዓይኔን እንደማታጠፍኝ እንዴት ኣቃለው? ኣንቺ እንደሌሎቹ የውሸት ነጋዴዎች ብትሆኝስ፣ ማለት ተስፋ እየሰጠሽ የምትዋሺ ብትሆኝስ?"
ንግግሩ መርዘም ጀመረ። "ምንም ላልጎዳኝ ፍጥረት እንደሱ ኣላደርግም እኔ።"
"ብጎዳሽስ ዓይኔን ታጠፍኛለሽ ማለት ነው?
"እሱ በማውቅ እና ኣስፈላጊንቱ የተመሰረተ ጉዳይ ነው የሚሆነው።"
"ስለዚ፣ እኔ ስላንቺ ለማንም ካልተናገርኩኝ፣ ኣንቺ ኣይኖቼን ካስተካከልሽልኝ፣ ፊልዶቻችን ትተይልንናለሽ፣ ማለት ነው?"
"ኣዎ፣ ዋና መልእክቱ እሱ ነው" [...]