[...] "አንድ ሀሳብ አለኝ።" ምንም እንኳን ከሚስጥሮቿ አንዱም እንኳን ጥሩ ወይም ደግሞ የአውነት ምስጢር ባይሆንም ጓደኛዬ ኤፕሪል ልክ ሚስጥር ለመናገር ስትፈልግ እንደምታደርገው ወደ ፊት ቀረብ አልኩ። "እኔ እዚህ መሆኔን ለማንም ካልተናገርክ ዓይኖችህን ማስተካከል እችላለሁ።"
"ከከተማ ውጣ!"
ሁለት ጊዜ ብልጭ ድርግም አለ። "ያንን ለማድረግ ነው እየሞከርኩ ያለሁት።"
"እያልኩ ያለሁት ይህን ማድረግ አትችልም ነው!"
"ለምን አይሆንም?"
"እሺ፣ በመነፅር ነው አንጂ ከዛ ውጪ ዓይኖቼን ማስተካከል የቻለ ማንም አልነበረም።"
"አንዳንድ ችሎታዎች አሉኝ። ታያለህ፣ እንዳልኩህ …”
"...ስለ አንተ ለማንም አልናገርም?"
"የነገሩ ልብ ያ ነው፣ ዋናው ነገር ያ ነው።"
"እንደማታሳውረኝ በምን አውቃለሁ? አንደነዚያ ቃል እየገቡ ከሚዋሹት የበይነመረብ ነጋዴዎች መካከል እንደ አንዱ ልትሆን ትችላለህ።"
ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት እያሰበ በድጋሚ መብሰልሰል ጀመረ። "ምንም ጉዳት ያላደረሰብኝ ፍጡር ላይ እንዲህ ዓይነት ነገር አላደርግም።"
“አንተን ከጎዳሁህ ታሳውረኛለህ ማለት ነው?”
"እሱ ጊዜና ሰዓቱ ሲደርስ የምናውቀው ይሆናል።"
"እና ዓይኖቼን ካስተካክል እና እኔም ስለ አንተ ለማንም ካልነገርኩ፣ እርሻችንን ትተህ ትወጣለህ?"
"የነገሩ ልብ ያ ነው!" [...]